የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት ተግባራት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ አካሄደ።
በመድረኩ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች የዞን ቡድን መሪዎች፣ ሠራተኞች እንዲሁም የየወረዳው እቅድ ዝግጅት ቡድን መሪዎች ገኝተዋል።
መድረኩን ያስጀመሩት አቶ ግዛቸው ነገሠ እንደተናገሩት በ2017 በጀት አመት ምንም እንኳን በሰላም እጦት ውስጥ የነበርን ቢሆንም በችግር ውስጥ ሆነን ሰርተን እንደ ዞን መልካም ውጤት ማምጣት ችለናል ብለዋል።
ይህ ውጤት እንዲመጣ የአንበሳውን ድርሻ የምትወስዱት በአስተዳደር ጽ/ቤት ስር ያላችሁ አመራሮች፣ ቡድን መሪዎችና ሠራተኞች በመሆናችሁ በዞን አስተዳደሩ ስም ምስጋና ይገባችኋል።
በያዝነው 2018 በጀት አመትም የችግሩን አሳሳቢነት ከተለመደው አሰራር በላይ ከፍ ብለን ማየት እና አልቀን መስራት ይጠበቅብናል።
ስለሆነም ችግሩን፣ መለየት፣ መረዳት፣መመርመር፣ መተንተን ዋናውንችግር፣የችግሩን መንስኤ እና የችግሩን ውጤት አንጥሮ በማውጣት እንዳይደገም በቁርጠኝነት መስራት የህብረተሠቡን እርካታ ማሳደግ ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል ።
የ2017 በጀት አመት ተግባራት አፈፃፀም በመምሪያው እቅድ ዝግጅት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ደረጄ ጌታነህ የቀረበ ሲሆን በመድረኩ ፍፃሜ የተሻለ ለፈፀሙ አካላት የእውቅና መርሃግብር ተሰጥቷል።
በዚህ መሰረት ከወረዳዎች
1ኛ አንጎለላና ጠራ
2 ኛ መንዝ ጌራ
3 ኛ መርሐቤቴ
ሰርተፍኬት ተሸልመው መድረኩ ተጠናቋል።










Leave a Reply