የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ገመገመ።

በግምገማው ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ፣ የየክፍሉ የቡድን መሪዎችና ጠቅላላ ሠራተኞች ተገኝተዋል፣

በእለቱም በመ/ቤቱ የእቅድ ዝግጅት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ደረጄ ጌታነህ አማካኝነት በሩብ አመቱ በእቅዱ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ተግባራትን አቅርበው ሠፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ በሩብ አመቱ ከታቀዱት ተግባራት መካከል በርካታ ስራዎች በተሻለ አፈጻጸም መከናወናቸውን የገለፁ ሲሆን አክለውም በጥንካሬ የተከናወኑትን ተግባራት በማስቀጠል ፤ ታቅደው ሙሉ በሙሉ ያልተከናወኑ አፈፃፀሞች ላይ ሙሉ አቅምን በመጠቀመ መፈፀም እንደሚገባና በተለይም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ የቅሬታ አፈታትና የአገልግሎት አሠጣጥ ላይ ትኩረት በመስጠት ህብረተሠቡን ማገልገል እንደሚገባ በማሳሰብ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *