የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፅ/ቤት በዞኑ ካሉ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት እና ከንቲባ ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በ2018 በጀት ዓመት በ5 ወሩ የተከናወኑ ተግባራትን የገመገመ ሲሆን
በመድረኩ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሰአዳ ኢብራሂም ተገኝተው አስተያየት ሰጥተዋል።
በደንብ ቁጥር 78/2003 በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት በተቋሙ ስር የተደራጁ የፕላንና ልማት ቡድን ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን ፣ የሲቢልና ቤተሰብ ምዝገባቡድን ፣ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንዲሁም የስነ- ምግባር ቡድን ዘርፍ መከናወን ባለባቸው የተቋሙ ዋና ዋና ፒላር ላይ የተቋሙ ዕቅድና በጀት ዝግጅት ክ/ግምገማ ባለሙያ በሆኑት አቶ ደረጄ ጌታነህ አማካኝነት በ5 ወሩ በጥንካሬና በድክመት ለውይይት የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ፦
በመጨረሻም በዞኑ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ አማካኝነት በቀጣይ ትኩረት በሚሰጣቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ ውይይቱ ተጠናቋል።










Leave a Reply