Skip to content

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የሶሽዮ-ኢኮኖሚ ፕሮፋይል

ክፍል አንድ

1.      የመልክዓ– ምድር ሁኔታ

በዚህ ክፍል የዞኑን ገፀ-ምድር ሁኔታ የሚያመለክቱ የተለያዩ መረጃዎች ተዘርዝረዋል የዞኑ የመሬት አቀማመጥ ፣ አስተዳደሪዊ ክፍፍል መልክዓ-ምድር አወቃቀር ወንዞች ፣ ተራሮች ፣ የአየር ንብረት ክፍፍሎች ተካተዋል ፡፡

1.1.          የመሬት አቀማመጥና አስተዳደራዊ ክፍፍል

የሰሜን  ሸዋ  ዞን  በአማራ ብሄራዊ  ክልል ከሚገኙት  14 ዞኖች  መካከል  አንዱ  ሲሆን       የ 15795.9 ካሬ ኪ/ሜትር የቆዳ ስፋት ይዟል፡፡ ከክልሉ የቆዳ ስፋትም የ10.16% ድርሻ አለው፡፡ የዞኑ አቀማመጥም በቀጥታ አቅጣጫ ሰሜን ላቲቲውድ በ8.38-10.420 እና ምስራቅ ሎንግቲዩድ ከ38.4- 40.30ላይ የሚገኝ ሲሆን በተነፃፃሪ አቅጣጫ ደግሞ በደቡብ እና ምዕራብ ከኦሮሚያ ክልል ፣ በሰሜን ከደቡብ ወሎ ፣ በሰሜን ምስራቅ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ፣ በምስራቅ ከአፋር ክልል ይዋሰናል፡፡                                

ስዕል 1   የሰሜን ሸዋ ዞን የመሬት አቀማመጥ እና አስተዳደራዊ ክፍፍል ካርታ

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደራዊ ክፍፍልን በተመለከተ በ22 የወረዳዎች እና 9 ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም 371 የገጠር 52 የከተማ በድምሩ 423 ቀበሌዎች ይገኛሉ፡፡ አስተዳደራዊ ክፍፍሉ መሠረት ያደረገው ተፈጥሮአዊ ፣ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን ሲሆን (ከእነዚህም ዋናዎቹ የቆዳ ስፋትና ርቀት ናቸው) ለህዝቡ ቀልጣፋ ፣ ፍትሃዊና ተደራሽ አገልግሎቶችን ለመስጠት የክልሉ መንግስት እንደ አስፈላጊነቱ የአስተዳደር ክፍፍልን በተለይ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ በየጊዜው ሲሻሻል ቆይቷል ወደፊትም ሊሻሻል ይችላል፡፡

ሰንጠረዥ 1የወረዳዎች የቀበሌ ብዛት በገጠርና በከተማ

ተ.ቁወረዳየቀበሌ ብዛት
የገጠር የቀበሌየከተማ የቀበሌድምር
1መርሐ ቤቴ23124
2ዓለም ከተማ አስተዳደር033
3አንጎለላ ጠራ16117
4አንኮበር19423
5አንፆኪያ ገምዛ11112
6አሣግርት14115
7ኢፍራታና ግድም24327
8አጣዬ ከተማ አስተዳደር033
9በረኸት9110
10ባሶና ወራና21021
11እንሣሮ13114
12ግሼ ራቤል11112
13ሀገረ ማርያምና ከሠም19120
14ቡልጋ ከተማ አሰተዳደር011
15ቀወት18220
16ሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደ.459
17መንዝ ጌራ ምድር20020
18መሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደር044
19መንዝ ቀያ12113
20መንዝ ላሎ ምድር718
21መንዝ ማማ ምድር19019
22ሞላሌ ከተማ አስተዳደር011
23ሚዳ ወረሞ20323
24ምንጃርና ሸንኮራ26127
25አረርቲ ከተማ አስተዳደር123
26ሞጃና ወደራ13316
27ሞረትና ጅሩ19120
28እንዋሬ  ከተማ አስተዳደር011
29ሲያደበርና ዋዩ13114
30ጣርማ በር18119
31ደብረ ሲና ከተማ አስተዳደር134
ድምር37152423

ሰንጠረዥ 2  የወረዳዎች የቆዳ ስፋት እና የወረዳው ዋና ከተማ  ከክልል እና ከዞን ማዕከል ያለው ርቀት

የዞንና የወረዳ ስምየወረዳው ዋና ከተማየወረዳው የቆዳ ስፋትየወረዳው ዋና ከተማ
በካሬ ኪ.ሜበሄክታርከዞን ያለው ርቀት በኪ.ሜከባ/ዳር ያለው ርቀት በኪ.ሜ
ሰሜን ሸዋደብረ ብርሀን15795.91579590.84  
መርሐ ቤቴዓለም ከተማ917.8791787.26142 598
ዓለም ከተማ አስተዳደር›lM kt¥50.765076.81142 598
አንጎለላ ጠራጫጫ673.467340.8020673
አንኮበርጎራቤል730.9473093.8042735
አንፆኪያ ገምዛመኮይ37537500.50220783
አሣግርትጊናግር509.6350963.3075768
ኢፍራታና ግድምአጣዬ464.1846418.23139832
አጣዬ ከተማ አስተዳደርxÈü36.893688.94139725
በረኸትመተህብላ812.6881267.57164773
ባሶና ወራናደብረ ብርሀን828.3182830.510.0 695
እንሣሮለሚ435.8243581.9083534
ግሼ ራቤልራቤል675.8567585.07262737
ሀገረ ማርያምና ከሠምሾላ ገበያ655.8765586.8380685
ቡልጋ ከተማ አሰተዳደርቡልጋ71.587158.4163632
ቀወትሸዋ ሮቢት625.7662576.1395790
ሸዋ ሮቢት ከተማ አስተዳደ.¹ê ébþT146.3214631.7295790
መንዝ ጌራ ምድርመሀል ሜዳ1072.72107271.54157854
መሀል ሜዳ ከተማ አስተዳደርmhL »Ä31.893189.43157854
መንዝ ቀያዘመሮ587.6158761.43189750
መንዝ ላሎ ምድርወገሬ363.8236381.88145830
መንዝ ማማ ምድርሞላሌ637.6863768.44124809
ሞላሌ ከተማ አስተዳደርሞላሌ28.712871.30124809
ሚዳ ወረሞመራኛ850.7185071.44191639
ምንጃርና ሸንኮራአረርቲ1,688.28168828.27172700
አረርቲ ከተማ አስተዳደርአረርቲ56.235623.23172700
ሞጃና ወደራሠላ ደንጋይ625.2962528.9472757
ሞረትና ጅሩእንዋሬ681.7868178.1365567
እንዋሬ  ከተማ አስተዳደርእንዋሬ24.382437.5265567
ሲያደበርና ዋዩደነባ508.4250841.9747554
ጣርማ በርደብረ ሲና590.4259041.7460745
ደብረ ሲና ከተማ አስተዳደርደብረ ሲና37.083707.8060745

ምንጭ፡-የወረዳዎች ልማት ዕ/ክ/ግ/ ቡድን

በዞኑ ከሚገኙ ወረዳዎች ከተማ አስተዳደሮች መካከል የምንጃርና ሸንኮራ ወረዳ በ1,688.28 ካ/ኪ/ሜትር በመሸፈን ከፍተኛውን የቆዳ ስፋት የያዘ ሲሆን ከዞኑ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት10.6 በመቶ ድርሻ ያለው ሲሆን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር 24.38 ካ/ኪ/ሜትር በመሸፈን ዝቅተኛውን የቆዳ ስፋት ይዟል፡፡በዚህም እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከዞኑ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 0.15በመቶ ድርሻ አለው፡፡

1.2 መልክዓምድራዊ አወቃቀር

የመሬት ቅርፅና ገፅታ በረጅም ጊዜ ሂደት የተከሰቱ የልዩ ልዩ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ውጤት ነው ፡፡ ከእነዚህም መካከል የከርሰ-ምርድ ንቅናቄ ፣ የአየር ፀባይ ፣ የመሬት መሸርሸርና የመሬትስበት ይገኙበታል፡፡በዞኑ የአሁኑን የመሬት-ገፅ በአብዛኛው የከርሰ-ምድር ንቅናቄ ፣ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የመሬት መሰንጠቅና የእሣተ-ገሞራ ውጤት ናቸው፡፡ በመሆኑም የዞኑ የመሬት ገፅታ የተለያየና ወጣ ገባ ፣ ሸለቆ ፣ ተራራ እና ሜዳማነት የሚታይበት ነው፡፡  እንዲሁም በደን የተሸፈኑና የተራቆቱ መልክዓ-ምድሮች ይገኙበታል ፡፡

የዞኑ ህዝብ በአብዛኛው የሠፈረው ወይናደጋ እና በደጋማው  አካባቢ ሲሆን በትናንሽና በተበጣጠሰ የእርሻ መሬቶች በሚገኝ የግብርና ምርት ከእጅ ወደ አፍ በሆነ የኑሮ ደረጃ የሚገኝ ነው ፡፡ በዞኑ የሚገኘው ቆላማ አካባቢ በሀገራችን የማህበራዊ አገልግሎቶች እና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች  ባልተስፋፋበት ወቅት የውሃ እጥረት እና የጤና ቀውስ በሚያስከትሉ ተባዮች /በዋነኛነት የወባ ትንኝ /አከባቢው ተጋላጭ ከመሆኑ የተነሳ በአንፃራዊነት ብዙ ህዝብ አልሠፈርበትም ማለት ይቻላል፡፡      

                     1.2.1  የሥነ-ምህዳር አወቃቀር

በአጠቃላይ ዞኑ በአራት ዋና ዋና የመሬት አወቃቀር ምድብ የሚከፈል ሲሆን እነዚህም ውርጭ /ቁር/ ፣ ደጋ ፣ ወይና ደጋ እና ቆላ ናቸው፡፡

ደጋ፡- ይህ አካባቢ ከባህር ወለል በላይ ከ2500 እስከ 3500 ሜትር ከፍታ የሚገኙና በቀዝቃዛ የአየር ፀባይ ፣ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ፣ በአንጻራዊነት ባለው የደን ሽፋን መጠን የሚታወቅ ቢሆንም በአሁኑ ጊዜ ባለው የእርሻ መሬት ፍላጎት ደንና ቁጥቋጦው በመመንጠር ላይ ይገኛል ፡፡ከዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 32.02%ያህል በዚህ ከፍታ ውስጥ ይገኛል፡፡

ወይናደጋ፡- በአማካይ ከባህር ወለል በላይ ከ1500 እስከ 2500 ሜትር ከፍታ ያለውን ስፍራ የሚሽፍን ሲሆን ከዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ከፍተኛው ወይም 45.58 በመቶ ድርሻ ይይዛል ፡፡የመሬቱ  አቀማመጥ ብዙም ወጣገባነት የሌለው በመሆኑ ለእርሻ እና ለእንስሳት እርባታ አመቺ ያደርገዋል ፡፡መካከለኛ ሙቀትና በቂ ዝናብ የወይና ደጋ መገለጫ ባህርያት ናቸው ፡፡

ቆላ ፡- ከባህር ወለል በላይ ከ500 እስከ 1500 ሜትር ያለው ከፍታ መጠሪያ ሲሆን ከዞኑ 21.95 በመቶ የሚሆነው በዚህ ምድብ ይካተታል ፡፡ነው፡፡ የመሬቱ  አቀማመጥ  በአብዛኛው ሸለቋማ እና ዝቅተኛ ሲሆን በምስራቅ በኩል ዞኑን ከአፉር ክልል እና በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ከኦሮሚያ ክልል በሚለየው ወሰን በኩል ያለው ሜዳማ ሲሆን በዝናብ ዕጥረት  እና ከፍተኛ ሙቀት  የሚታወቅ ነው፡፡

ውርጭ/ቁር/፡- በአማካይ ከባህር ወለል በላይ ከ3200 እና በላይ ሜትር ከፍታ ያለውን ስፍራ የሚሽፍን ሲሆን ከዞኑ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ዝቅተኛው ወይም 0.46 በመቶ ድርሻ ይይዛል፡፡የመሬቱ አቀማመጡ በዞኑ በሚገኙ ከፍተኛ ተራራዎች አካባቢ በተለይም በመንዝ እና ግሼ  በባሶና ወራና አንኮበር እና አሣግርት ወረዳዎች የሚገኝ ሲሆን አካባቢው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እና ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሚታወቅ ነው፡፡

                    ስዕል 2  የሥነ-ምህዳር አወቃቀር ካርታ

1.2.2 የመሬት ተዳፋትነት

የመሬት ተዳፋትነት ለእርሻ ሥራ &ለመሠረተ-ልማት እና ማህበራዊ አገልግሎት የመሳሰሉትን ለማስፋፋት ወሣኝ ሚና ይጫወታል፡፡የሰሜን ሸዋ ዞን የመሬት አቀማመጥ በጣም ተዳፋታማ በመሆኑ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለማሟላት አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ የዞኑ የመሬት ተዳፋትነት መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 3 የዞኑ የመሬት ተዳፋትነት

ተ.ቁየተዳፋትነትበመቶኛ
10—23.33
22—829.29
38—1628.77
416—3232.76
5>3211.9

           ስዕል 3  የዞኑ የመሬት ተዳፋትነት ካርታ

1.3 በዞኑ የሚገኙ ወንዞች

በሰሜን ሸዋ ዞን በርካታ ዋና ዋና ወንዞች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ወንዞች በዋናነት በአባይና በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ ሥር የሚመደቡ ሲሆን ከሚሰጡት ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አንፃር አብዛኞቹ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫነት እና ለመስኖ ልማት መዋል የሚችሉ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ስለሆነም  የእያንዳንዳቸውን ወንዞች ዝርዝር ጠቀሜታቸውን በሚመለከት የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለሀብቶች  ሰፊ ጥናት እንዲያደርጉበት እና በዘርፉ እንዲሰማሩ ሁኔታው ይጋብዛል፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ወንዞች በዞኑ ጎልቶ ለሚታየው የአፈር መሸርሸር የራሳቸውን ድርሻ እንዳላቸው ግልፅ ነው፡፡

ሰንጠረዥ 4 በዞን የሚገኙ ዋና ዋና ወንዞች፣ ግምታዊ ርዝመታቸውና ተፋሰሶቻቸው

ተ.ቁወረዳ/ወንዝተፋሰስግምታዊ ርዝመት በኪሎ ሜትር
ባሶና ወራና
1ጉናጉኒትጥቁር አባይ  N.A
2ለገዳ     »     »
3ወርቄ     »     »
4ፍልቁ ወንዝ     »     »
5ሙሽ ወንዝ     »     »
6በሬሣ     »80
7አንጓ መስክ     »  N.A
አንጎለላናጠራ
1ጫጫጥቁር አባይ75
አንኮበር
2መልካጀብዱአዋሽ  N.A
3አይራራ     »     »
4ጭብጤ     »     »
5ድንኪ     »     »
6ጨውበሌ     »     »
ሀገረማርያም
1ከሰምአዋሽ110
በረኸት  
1ከሰምአዋሽ110
2ቆሬ     »  N.A
ኢፍራታናግድም
1ጀወሃአዋሽ  N.A
2ናዛሮ     »     »
3አዘራ     »     »
4ጃራ     »     »
አንፆኪያ ገምዛ
1ጉዳበርአዋሽ  N.A
2ዳሪጋ     »     »
መንዝ ጌራ
1ቀጭኔጥቁር አባይ  N.A
2ሻይ     »     »
3ገደምቦ     »     »
ግሼ
1ቀጭኔጥቁር አባይ  N.A
መርሀቤቴ
1ጀማጥቁር አባይ110
2ወንጭት     »135
ቀወት
1ጉንፋታአዋሽ  N.A
2ሰውር     »     »
3ሮቢ     »     »
4ጀወሃ     »     »
መ/ማማ
1ሞፈር ውሃጥቁር አባይ43
ሞረትናጅሩ
1ጀማጥቁር አባይ  N.A
ምንጃርሸንኮራ
1ሸንኮራአዋሽ  N.A
2ከሰም     »75
ሚዳወረሞ
1ጃራጥቁር አባይ  N.A
2ወንጭት     »135
3በቶ     »  N.A
ሲያደብርናዋዩ
1ሮቢጥቁር አባይ  N.A
ጣርማበር
1አዋዲአዋሽ  N.A
ሞጃናወደራ
1ከስካሽጥቁር አባይ  N.A
2አይሰራውም     »     »
አሣግርት
1መንጥርአዋሽ  N.A
2አምቱ     »     »
3ቆሬ     »     »
መንዝቀያ
1ወንጭትጥቁር አባይ135
2ጀማ     »110
3ሻይ     »     »
መንዝላሎ
1አዳባይጥቁር አባይ  N.A
2አፍቃራ     »     »
እንሣሮ
1ጀማጥቁር አባይ110
2ዜጋወደም     »  N.A
3ሮቢ     »     »
ደ/ብርሃን
1በሬሣጥቁር አባይ80
ሸዋሮቢት  
1ሮቢአዋሽ  N.A
2ቆቦ     »     »
አጣዬ ከተማ አስተዳደር
1ናዛሮአዋሽ  N.A

ምንጭ፡-የወረዳ ልማት ዕቅድ ክ/ግ/ ቡድን

  1.4 በዞን የሚገኙ ተራሮች

በሰሜን ሸዋ ዞን የበርካታ ተራሮች ይገኛሉ፡፡ በዞኑ የሚገኙት ተራሮችም በጣም ከፍተኛ ቅዝቃዜ /ውርጭ/ ፣ በአንፃራዊነት ከፍተኛ የዝናብ መጠን እና ከፍተኛ የንፋስ ኃይል እንዲሁም የብርቅዬ አራዊት መነኸሪያ መሆናቸው የነዚህ አካባቢዎች የተለዩ ባህርያት ናቸው፡፡ ስለሆነም ተራሮቹ ከሚሰጡት የኢኮኖሚ ጥቅም አንፃር ለቱሪዝም እና ለንፋስ ኃይል ማመኝጫነት መዋል የሚችሉ ናቸው

ሰንጠረዥ 5 በዞኑ የሚገኙ ዋና ዋና ተራሮች እና ከፍታቸው በወረዳ

.ቁየተራራው ስምከፍታው በሜትርየሚገኝባቸው ወረዳዎች
1አቤላምN.Aባሶና ወራና
2ቀራማርያምN.A     »
3ጎሽ ሜዳN.A     »
4ገማሣ ገደልN.A     »
5እመምረትN.Aአንኮበር
6ቁንዲ3000     »
7ችሳኝN.Aሀገረማርያም
8የቁርN.A     »
9ጓሣ3400መንዝ ጌራ
10ፍየል ግምባር3000ግሼ
11ጭራገብርኤል3159     »
12አቡየሜዳ4000     »
13ገራውጊያ3450     »
14ጉበኛ3388     »
15ገለምቲት3234     »
16መገዘዝ3596አሣግርት
17 ጣርማበርN.Aሞጃናወደራ
18ራሣ ጉባ3200ቀወት
19ጋራድንቁN.Aደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር

ምንጭ፡-የወረዳ ልማት ዕቅድ ክ/ግ/ ቡድን

N.A መረጃ አልተገኘም

N.A Data is  not available

1.5 የተፈጥሮ እፅዋት

የተመሣሣይ ዕፅዋት ስርጭትን ፣ የዝናብ መጠንን ፣ የአፈር ለምነትንና ለማዳን የሚፈጅባቸውን የጊዜ ርዝመት መሠረት በማድረግ በዞኑ የሚገኙት የተፈጥሮ ዕፅዋት በሚከተሉት ቀጠናዎች ተከፍለዋል ፡፡ይህ የቀጠና ክፍፍል ፖሊሲ አምጭዎች የተለያዩ የእርሻና የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴዎች እንዲነድፉ ይረዳል፡፡

ኮኒፈረስ ደን /coniferous forest/ በዞኑ ካለው የደን ሃብት ከፍተኛ ድርሻ /91.22%/ ያለው ሲሆን በሁለቱም ማለትም በከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎች ጁኒፕረስ /Juniperous/ በዝቅተኛ ቦታዎች ደግሞ ፓዳካርፐስ /podicarpus/ በመባል የሚታወቁት የዕፅዋት ዝርያዎች የመሬት ገፅታው መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ከ200 እስከ 1300 ሚሊ ሜትር ሲሆን የማብቂያ/ማደጊያ ወቅትም ከ1 እስከ 12 ወራት ይደርሳል፡፡መጠነኛ እርሻ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የአፈር ለምነት ከፍተኛ ሲሆን መጠነ ሰፊ እርሻ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የአፈር ለምነት ዝቅተኛ ነው፡፡ይህ ቀጣና እንደ ቀንድ ከብቶች ፣ በጐችና ፍየሎች ያሉትን እንሰሳት ለማርባትና ለደን ልማት በዋነኛነት አመቺ ነው፡፡

ደን ለበስ ሳቫና /Woodland savannah/:- ይህ ቀጣና በጁኒፐርስ ግራር /Juniperous Acacia/ እና በክረምት ወራት ቅጠላቸውን በሚያራግፉ ዛፎች /Deciduous Woodland/ በሣር በተሸፈነ ቁጥቋጧማ ዕጽዋት /Grassland and Shrub Vegetation/ገጽታው ይታወቃል፡፡ አማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን  ከ200 እስከ 1400ሚሊ ሜትር ሲደርስ የዕፅዋት መብቀያ /ማደጊያ ወቅት እስከ 10 ወራት ይሆናል፡፡አካባቢው ለዱር አራዊት ጥበቃና ልማት & ለሠፈራ ፕሮግራም ና ለአከባቢ ጥበቃና ልማት ምቹ ሲሆን በሰሜን ሸዋ ዞን የሚሸፍነው  የደን ሀብት  8.78 በመቶ ብቻ ነው፡፡

አፍሮ አልፖይን እና ሰብ አፍሮ አልፖይን /Afro alpine and Sub-afro alpine) ተብሎ የሚጠራ  እንዲሁም ባለሰፋፊ ቅጠል ደን /Broad leafed Forest/ የሚባል በሰሜን ሸዋ ዞን ባለመኖራቸው በዚህ ክፍል ውስጥ አልተገለጹም፡፡

ሰንጠረዥ 6 የሰሜን ሸዋ ዞን የተፈጥሮ እፅዋት ክፍፍል

የተፈጥሮ ዕፅዋትበመቶኛ
አፍሮ አልፖይን እና ሰብ አፍሮ አልፖይን /Afro alpine and Sub-afro alpine)0.00%
ኮኒፈረስ ደን /coniferous forest/ 91.22%
ባለሰፋፊ ቅጠል ደን /Broad leafed forest/0.00%
ደን ለበስ ሳቫና /Woodland savannah/8.78%
  

1.6 የማዕድን ሀብቶች

ማዕድናት የተወሰነ የኬሚካላዊ ቅንብር ሲሆን እያንዳንዳቸው ከተወሰኑ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ድብልቅ የተሠሩ ናቸው፡፡ ማዕድናት የታዘዘ የአቶሚክ አደረጃጀት ያላቸው ሲሆን እያንዳንዱ ማዕድንናት ከሚያካትቱት ኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮች ይመደባሉ። በዚህም በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ የማዕድን ክምችት በወረዳ በሚከተለው ሰንጠረዥ ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 7 ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኝ ማዕድን ክምችት በወረዳ

ተ.ቁየማዕድን ዓይነትየሚገኝበት ወረዳየክምችት መጠን
1ጀሶ ድንጋይበጅማ ወንጭት ወንዞች       አካባቢ መርሃቤቴ ፤እንሳሮ፣ ሞርትና ጅሩ ፤ሀ/ማሪያምበብዙ ሚሊዮን ቶን የሚገመት
2ሲልክ ሳንድሰ/ሸዋ ጀማ ወንዝ አካባቢ መርሃቤቴ፤እንሳሮ እና ሚዳ ወረሞበጥናት ላይ ያለ
3ሸክላ አፈር /ከለተይ/የዞናችን ሁሉም አካባቢዎችበሚፈለገው መጠን ይገኛል
4ኖራ ድንጋይበመርቤቴ፣ሚዳወረሞ፣ እንሳሮ ፣ሞረትና ጅሩ በጀማና ወንጭት ወንዞች አካባቢበብዙ ሚሊዮን ቶን የሚገመት
5የድንጋይ ከሰልባሶናወራና( ሙሽ) እና አንኮበር0.3 ሚሊዮን ቶን
6ብረትግሼ፤ባሶናወራና(ሙሽ) እና አንኮበርአይወቅም
7ቀይ አሸዋምንጃርመጠኑ የማይታወቅ
8የሙቅ ዉሃ ጂኦተር ማል ክምችትሸዋሮቢትአይታቅም
9የማዕድን ውሃ ክምችትደ/ብርሃን፤ አን/ጠራ፤ ሸዋሮቢት እና በብዙዎች ደጋማ ወረዳዎች በበቂ መጠን
10ፑሚስ/ባሃ ድንጋይ/ምንጃር ሸንኮራ አካባቢበብዙ ሚሊዮን ቶን የሚገመት
11ኢግንም ብራይትበብዙዎቹ ወረዳዎችመጠነ ሰፊ ክምችት
12ግራናይትደ/ብርሃንና በዙሪያውበአስተማማኝ የክምችት መጠን የሚገመት
13ዶሎማይትምንጃር ፣መ/ቤቴ እና እንሳሮበጥናት ላይ ያለ
14ኦፓልጣርማበር ፣ኢፍራታናግድም እና መንዝ ማማበጥናት ላይ ያለ
15አምበርመንዝ ማማበጥናት ላይ ያለ

1.7  የእምነት አወቃቀ

ሰንጠረዥ 8 የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ የእምነት ስብጥር በመቶ

የሀይማኖት ስብጥርበመቶኛ
ኦርቶዶክስ94.71
ፕሮቴስታንት0.35
ካቶሊክ0.01
ሙስሊም4.91
ባህላዊ0.01
ሌሎች0.01

ምንጭ፡-ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ

1.8  የብሄር ስብጥር

ሰንጠረዥ 9 የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ የእምነት ስብጥር በመቶኛ

የብሄር ስብጥርበመቶኛ
አማራ96
ኦሮሞ2
አርጎባ2

ምንጭ፡-ማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲ

ክፍል ሁለት

የስነ-ህዝብ ሁኔታ

እንደ ሰሜን ሸዋ ዞን ፕላን ኮምሽን ስነ ህዝብ መረጃ በ2016 የበጀት አመት 2,231,205 ህዝብ በዞኑ ይኖራል ተብሎ ይገመታል። ከዚህ  ውስጥ 1,148,571 ወንዶች  ሲሆኑ 1,082,634 ሴቶች ናቸው። በተጨማሪም 17.5% የከተማ ነዋሪ ሲሆን 82.5% የገጠር ነዋሪ ነው። በዞኑ ካለው ህዝብ 38.6% የሚሆነው ከ15 አመት በታች & 5.1% የሚሆነው ደግሞ ከ64 ዓመት እድሜ ክልል በላይ  ሲሆን ከ15 — 64 ዓመት ዕድሜ ክልል/አምራች ሃይል የሚባለው 56.3 በመቶ መሆኑን መረጃው ያሣያል፡፡በተጨማሪም በዞኑ ከሚገኙት ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ ትልቁን የህዝብ ቁጥር የያዘው ኢፍራታ ግድም ወረዳ  ሲሆን ትንሹን የህዝብ የያዘው ደግሞ የቱለፋ ከተማ አስተዳደር ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *