Skip to content

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን በኢትዮ-ኮደርስና ከ1ኛ-3ኛ ዙር ለመንግሥት ሠረተኞች በመሠረታዊ የኮምፒዩተር ሙያ ላሠለጠናቸው ሠልጣኞች የዕውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን በኢትዮ-ኮደርስና ከ1ኛ-3ኛ ዙር ለመንግሥት ሠረተኞች በመሠረታዊ የኮምፒዩተር ሙያ ላሠለጠናቸው ሠልጣኞች የዕውቅና ሠርተፊኬት ሰጠ።

ደብረ ብርሃን፦ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም (ሰሸዞአስ) በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን በኢትዮ-ኮደረስ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የዞን ተቋማት፣ ለወረዳና ከተማ ከስተዳደሮች የሠርተፊኬት ዕውቅና የተሠጠ ሲሆን ቡድኑ ከ1ኛ-3ኛ ዙር ከ130 በላይ የመንግስት ሠራተኞችን በመሠረታዊ ኮምፒዩተር ሙያ ላሰለጠናቸው ሠልጣኞችም የዕውቅና ሠርተፊኬት ሠጥቷል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ልህቀት ዲዛይንና ቁጥጥር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብረሃም አያሌው መልእክት አስተላልፈዋል።

ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ሁሉም ሰው የቴክሎጂ ፋይዳና ጥቅም በውል በመረዳት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ ኢብራሂም ጨምሮ የዞኑ የየመምሪያ ኃላፊዎች ፣ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች ተገኝተዋል።

የዞኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይ አገልግሎት አሠጣጡን ከኋላ ቀር አሠራር ለማላቀቅ መረጃን በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠትና ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ ስልጠና የተሠጠ መሆኑን ገልፀዋል።

አያይዘውም የኢትዮ-ኮደርስ ዜጎችን የዲጅታል ክህሎት ከማሳደግ ባሸገር የሥራ ዕድል የሚያስገኝ መሆኑን ገልፀው በ5 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ በአጠቃላይ በዞናችንና በክልላችን በተደረገ ጥረት እስካሁን 103 ሺህ ዜጎች የኮደርስ ስልጠናውን የወሰዱ መሆኑን መረጃ ያመለክታል በማለት በአመቱ ቀጣይ ወራቶች ሁላችንም በቅንጅት ርብርብ በማድረግ የዞናችን ወጣቶች ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል በማለት የእለቱ የዕውቅና ፕሮግራም ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *