የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን የ10 ወር የስራ አፈፃፀምና የቀጣይ አቅጣጫን በቨርቺዋል ቪዲዮ ኮንፈረንስ ገመገመ፣
በአብክመ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን የ10 ወር እቅድ አፈፃፀም በቨርቺዋል ቪዲዮ ኮንፈረንስ የገመገመ ሲሆን ውይይቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ፣ የዞኑ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይና የየዘርፉ አስተባባሪዎች መርተውታል።
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱም ላይ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና አጠቃላይ የቡድኑ ሠራተኞች ተሳትፈዋል ።
በ10 ወሩ እቅድ አፈፃፀም ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘገቡትን ውጤት ማሳየት የተቻለ ሲሆን በዚህም መሠረት፦
1ኛ. የግሼራቤል ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን
2ኛ. የአሳግርት ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን
3ኛ. የሞጃና ወደራ ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን ሲሆኑ
1ኛ. የጣርማበር ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን
2ኛ. የአንጎለላና ጠራ ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን
3ኛ. የአሳግርት ወረዳ አስ/ጽ/ቤት ኢ/ቴ/ ቡድን ናቸው።
በቀጣይ ወራት ትኩረት የሚደረግባቸውን ተግባራት ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል።


