የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት ሥራዎችን ገምግሞ የ2018 ዓ.ም የዕቅድ ትውውቅ አደረገ፦

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት ስራዎችን ሲገመግምና የ2018 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ሲያደርግ የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠን ጨምሮ የእቅድ ዝግጅት አስተባባሪ፣ የቡድን መሪዎችና አጠቃላይ ሠራተኞች በግምገማው ተገኝተዋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ ውይይቱን የከፈቱ ሲሆን የመስሪያ ቤቱ የዕቅድ ዝግጀት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደረጄ ጌታነህ የሁሉንም የስራ ቡድኖችና የስራ ዘርፎች ያካተተ ጥቅል ሪፖርት በዝርዝር በፓወር ፖይንት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በውይይቱም ለቀጣይ ስራ አፈፃፀም ልምድ እንዲቀሰምበትና ብርታት እንዲሆን በበጀት አመቱ በስራቸው ጠንካራና ደካማ ውጤት ያስመዘገቡ ቡድኖች ወረዳና ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤቶችን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም የዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የቡድን መሪዎችና የስራ ዘርፍ ተጠሪዎች አጠቃላይ ሠራተኞች ቢስተካከሉና ለቀጣይ ትኩረት ቢሰጧቸው ያሏቸውን ጉዳዮች አቅርበዋል፡፡

በቀረቡት ሃሳቦች ላይ የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሠ ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሠላምን በማስቀደም በዞናችን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት መልካም ተሞክሮ ሊወሰድባቸው የሚችሉ ስራዎች የተሰሩ ሲሆን በፕላን ኮሚሽን ቡድን፣ በወሳኝ ኩነቶች ቡድንና በኢ.ኮ.ቴ ቡድን፣ በእቅድ ዝግጅት ዘርፍ፣ በቅረታ ሰሚና አፈታት ዘርፍና በሰው ሃይል ዘርፍ በጥንካሬ የተሠሩ ስራዎችን አንስተው ለአብነት የመ/ቤታችን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊባክን የነበረን ከ18,620,288.00 ከአስራ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ብር በላይ ወጪን ማዳን የተቻለ ሲሆን ሂደቱ በተጨማሪም በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ከ36,000 በላይ ሠልጣኞች እንዲሰለጥኑና አለም አቀፍ ሰርተፊኬት እዲይዙ ማድረግ ችለዋል ያሉ ሲሆነ። በድክመት የተነሱ ሃሳቦችን በመያዝ በተለይም ዝቅተኛ አፈፃፀም የታየባቸውን ሥራዎች በማረም በሚቀጥለው 2018 በጀት አመት ሁላችንም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሌሎች ተቋማት አርዓያ በመሆን ህዝብን ማገልገል ይጠበቅብናል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። በመጨረሻም የመ/ቤቱ እቅድ ዝግጅትና ክትትል ግምገማ ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ ደረጄ ጌታነህ የ2018 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ አቅርበው ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *